መመገቢያ ስፍራዎች

መመገቢያ ስፍራዎች

ሠገነት የተሰኘው የመመገቢያ ሥፍራ በሆቴላችን 11ኛው ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሥፍራ ልዩልዩ የአውሮፓ ምግቦች ምርጫ የሚቀርብሎት ሲሆን፤ ምግቦን እያጣጣሙ ዙሪያ ገባውን የአዲስ አበባ ከተማ ዕይታ በመቃኘት ይደሰቱ!

ሎቢ ባርና የእንግዳ ማረፊያው በሆቴላችን የመጀመሪያው ወለል ላይ ይገኛል፡፡ እንግዶቻችን እንደምርጫቸው ሳንዱዊች፤ፒዛ ወይም ዲዘርት ከባር ሚኑ ላይ በማዘዝ በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጁት የኮክቴል አይነቶች ከአንዱ አይነት ጋር በማጣጣም መጠቀም ይችላሉ!

dinning

የጋርደን ሬስቶራንታችን በግቢው ውስጥ ከዋናው ሕንፃ በስተጀርባ/በስኋላ ከሚገኘው የአትክልት ሥፍራ ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ባህላዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ልዩልዩ ምግብ ዓይነቶች ዝነኛና የታወቀ ነው፡፡ እንደየፍላጎትዎ ማግቡን በማዘዝ በመረጡት ቀዝቃዛ ወይም ሙቅ መጠጦች በማወራረድ ይደሰቱ!

ዋቢ ሸበሌ ሆቴል

ታሪካዊዋ የአዲስ አበባ ከተማ ካላት መስህብ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እርካታ ሰጪ አገልግሎት በሆቴላችን ያገኛሉ፤ ንቁና ታዛዥ ሠራተኞቻችን እያንዳንዱን የሚያስፈልጎዎትን አገልግሎት ለሟሟላት ዝግጁ ስለሆኑ ለሥራም ሆነ ለመዝናናት ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን በመምረጥዎ ዕድለኛ ንዎት፡፡

ይጎብኙን

ሜክሲኮ ራስ አበበ አረጋይ ጎዳና
+251 115 315057
+251 115 518477 / 2024
info@wabeshebellehotel.com.et

አድራሻችን