መመገቢያ ስፍራዎች
ሠገነት የተሰኘው የመመገቢያ ሥፍራ በሆቴላችን 11ኛው ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሥፍራ ልዩልዩ የአውሮፓ ምግቦች ምርጫ የሚቀርብሎት ሲሆን፤ ምግቦን እያጣጣሙ ዙሪያ ገባውን የአዲስ አበባ ከተማ ዕይታ በመቃኘት ይደሰቱ!
ሎቢ ባርና የእንግዳ ማረፊያው በሆቴላችን የመጀመሪያው ወለል ላይ ይገኛል፡፡ እንግዶቻችን እንደምርጫቸው ሳንዱዊች፤ፒዛ ወይም ዲዘርት ከባር ሚኑ ላይ በማዘዝ በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጁት የኮክቴል አይነቶች ከአንዱ አይነት ጋር በማጣጣም መጠቀም ይችላሉ!
የጋርደን ሬስቶራንታችን በግቢው ውስጥ ከዋናው ሕንፃ በስተጀርባ/በስኋላ ከሚገኘው የአትክልት ሥፍራ ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ባህላዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ልዩልዩ ምግብ ዓይነቶች ዝነኛና የታወቀ ነው፡፡ እንደየፍላጎትዎ ማግቡን በማዘዝ በመረጡት ቀዝቃዛ ወይም ሙቅ መጠጦች በማወራረድ ይደሰቱ!